ዓለምአቀፋዊ ዜና

የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ለ 5 ሺህ እስረኞች ምህረት አደረጉ

By Meseret Demissu

April 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሁሉ  የአንድነት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ 5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ  ታራሚዎች ምህረት አደርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ ከእስር የተፈቱት ታራሚዎች  ማህበረሰቡን እንደገና ሲቀላቀሉ ማረሚያ ቤት ያገኟቸውን ትምህርቶች በተግባር ላይ እንዲያውሉ እና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ አሳስበዋል ፡፡

የአንድነት በዓል ሚያዚያ 26 ቀን 1964 ታንጋኒካ እና ዛንዚባር ወደ  አንድነት በመምጣት የታንዛኒያ ሪፐብሊክን የመሰረቱበት ዕለት ነው ፡፡

በየዓመቱ በአንድነት በዓል ቀን ለታራሚዎች ምህረት ማድረግ የተለመደ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!