አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የፋሲለደስ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን የመማሪያ ክፍል ጥበት ችግር ለመቅረፍ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ ሁለት ደርብ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።
የመማሪያ ክፍል ህንጻው በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ትምህርት ቤቱ ከተማሪዎች ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ በአንድ ክፍል 100 በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር እንተገደደ ተገልጿል።
የጥምቀትን በዓል ለማክበር የመጡት የቀድሞ ተማሪዎችና ተወላጆች የፋሲል ከፍተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በሶዶ ለማ