የሀገር ውስጥ ዜና

የምግብ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ ተመረቀ

By Meseret Awoke

May 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን የምግብ ደህንነት እና ጥራትን ለመቆጣጠር ከ45 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያደራጀውን ዘመናዊ የምግብ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ አስመርቋል።

ቤተ ሙከራው የተለያዩ ምግቦችን ደህንነት በመመርመር ጥራታቸውን የማረጋገጥ አቅም እንዳለው ተገልጿል።

በምረቃው ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የቤተ ሙከራ አቅምን ማጎልበት የምግብ ደህንነት እና ጥራትን ለመቆጣጠር እና የህብረተሰቡን ጤንነት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ቤተ ሙከራው ሀገር ውስጥ የሚመረቱ እና የሚቀነባበሩ እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ ምግቦችን ጥራት እና ደህንነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸው፥ ቤተ ሙከራው በሀገሪቱ ያለውን የምግብ ጥራት እና ደህንነት በምርመራ በማረጋገጥ መረጃ ለማግኘት አጋዥ ነው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!