የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል የኮቪድ19 ነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከልን በድጋሚ ስራ ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደረሰ

By Tibebu Kebede

May 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል የኮቪድ19 ነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከልን በድጋሚ ስራ ለማስጀመር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት መስማማቱን አስታወቀ።

የጥሪ ማዕከሉ ከኮሮና ቫይረስ መረጃዎች በተጨማሪ ከወባ፣ ኩፍኝ ፣ ኮሌራ እና ማጅራት ገትር በሽታዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እንደሚያደርስ ይጠበቃል።

በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃ በተከናወነበት ወቅት ማዕከሉ ስራውን አቋርጦ የነበረ ሲሆን፥ በሳምንት እስከ 20 ሺህ የስልክ ጥሪዎች ሲቀበል እንደነበር ሺንዋ ዘግቧል።

የጥሪ ማዕከሉ ኮቪድ19ን ጨምሮ ሌሎች ጤና ነክ መረጃዎችን ከማቅረቡ ባሻገር፥ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የምክር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለጥሪ ማዕከሉ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ቁሳቁሶችን ከክፍያ ነፃ ያቀረበ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅትም የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!