አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡
ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ ተደርሶበታል፡፡
ይህ ቫይረስ “ብላክ ፒራሚድ ዋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል፡፡
ይህ ቡድን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመበርበር ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱም ታውቋል፡፡
በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ከኢመደኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!