የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻክር ፍላጎት የላትም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

By Tibebu Kebede

June 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻክር ፍላጎት እንደሌላት አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ኢትዮጵያ ዴሞካራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጀችበትና የተሻለ አካሄድን እየተከተለች ባለበት ወቅት የቪዛ ክልከላ አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም ብለዋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ ጉዳይ የኢትዮጵያ ትኩረትና ፍላጎት ነው ያሉት አምባሳደር ዲና፥ 120 አመታትን የተሻገረ ግንኙነት ያላቸውን ሀገራት ግንኙነት የማይመጥን አካሄድ ሊጤን እንደሚገባው አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ቻይናና ሩሲያ እያዞረች ነው በሚል የሚነሳው ሃሳብ የተሳሳተ መሆኑንና ከማንኛውም ሀገር ጋር ያላትን ግንኙነት የማጠናከር ቁርጠኝነት እንጅ ምርጫ ውስጥ የምትገባበት አካሄድ እንደሌለም አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም ሌላው ሃገር እስከፈለገና ብሄራዊ ጥቅምና ሰላማችን እስካልተነካ ድረስ ከማንኛውም ሃገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አንስተዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!