የሀገር ውስጥ ዜና

በሚኔሶታ ከሶማሌ ክልል ተወላጆች ጋር ውይይት ተደርጓል

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚኔሶታ ከሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ።

በክልሉ ልማትና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኡመር ፋሩቅ ጋር በመሆን ነው ውይይቱ የተካሄደው።

በውይይቱም ተወላጆቹ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ በመደገፍ ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ሲሆን፣ ይኸንኑ አጠናክረው ለመቀጠል ቃል መግባታቸውን በአሜሪካ የሚኔሶታና ሚድዌስት ቆንስላ ጀነራል አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሀመድ መግለጻቸውን ከጽ/ቤቱ የማህበራዊ ትስሰር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!