አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራዉ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዐት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመው ኮሚሽን ውይይት አካሂዷል፡፡
ኮሚሽኑ ሪፖርቱን ለማጠናቀቅ ከሁለተ ወር ያነሰ ጊዜ የቀረው ሲሆን፥ አባላቱ በሪፖርቱ ዝርዝር ይዘት ላይ የተወያዩበት ቁልፍ ስብሰባ መካሄዱን ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ታዋቂ ባለሙያዎችን ያቀፈ ሲሆን፥ ይፋዊ ክርክር፣ የፖሊሲ ውይይት ፣ የጋራ እርመጃዎችን የማያነሳሳ እና የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ምን መምሰል አለበት ለሚለዉ ዉይይት በር ከፋች የሚሆን ሪፖርት እያዘጋጀ ይገኛልም ነው የተባለው፡፡
ሪፖርቱ ለዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባኤ በህዳር ወር 2021 ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!