የሀገር ውስጥ ዜና

በ39 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በሀሮ በኮ ከተማ የተገነባውና 39 ነጥብ 3ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

ትምህርት ቤቱ በዘንድሮው ዓመት እንደ ክልል በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በጥራት እና በፍጥነት ለመገንባት እቅድ ይዞ ሲገነባቸው ከነበሩ 140 የኢፈ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው።

ትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጽሐፍት፣ ቤተ ሙከራ እንዲሁም የአስተዳደር ህንፃን ጨምሮ፥ ሌሎች ደረጃቸውን የጠበቁ ብሎኮች ያሉት መሆኑን የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጉዮ ገልገሎ ገልጸዋል።

የዞኑ አስተዳደርም ህዝቡን ጨምሮ በየደረጃው ካሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ትምህርት ቤቱ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን መቀበል እንደሚችል ተገልጿል ።

የአካባቢው ነዋሪዎችም ከዚህ ቀደም ከተማቸው ላይ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ወዳለበት ራቅ ወዳለ ስፍራ ለመላክ ሲገደዱ መቆየታቸውን በማንሳት የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!