አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ደኅንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩም ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለመስጠት እንዲንቀሳቀሱ የተደረገው የመጨረሻ ዝግጁነት ተገምግሟል፡፡
በዚህም የጸጥታ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሰማራ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ድጋፍ ለተለዩ እና ለሚከሠቱ አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ሥራ መሰራቱ ነው የተገለጸው፡፡
ሁሉም ዜጎች ነገ ድምፃቸውን ለመስጠት ሲወጡም አካባቢያቸውን በንቃት መከታል እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መንግሥትም የምርጫው ቀን ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!