አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)”ነገ ማልደን እንመርጣለን ” ሲሉ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የከተማዋ ኗሪዎች÷የምርጫ ካርዳቸውን ተጠቅመው ይበጀኛል የሚሉትን የፓለቲካ ፓርቲ እንደሚመርጡ ተናግረዋል ።
ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የሚጠበቅብንን ሃገራዊ ሃላፊነት እንወጣለን ብለዋል ።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ምርጫ ምክትል አስተባባሪ አቶ ብርቁ ሁነኝ ÷ምርጫውን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ለሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ደርሰዋል ነው ያሉት።
ቀደም ብሎ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ሰነድ ተዘጋጅቶ የጋራ ስራዎች ሲከናወኑ እንደቆየ ያነሱት አቶ ብርቁ÷ የጎላ እንከን አላጋጠመንም ብለዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን 1ሺህ 451የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን ÷18 ያህል የምርጫ ክልልሎች ይገኛሉ።
ነገ ሰኔ 14 ከማለዳ ጀምሮ ዜጎች ድምጽ ይሰጣሉ ።
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!