የሀገር ውስጥ ዜና

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እየተካሄደ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በሃገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።

በቀጣይ ተመሳሳይ መረጃዎችን ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው፣ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!