6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ተወካይ ሃላፊ ኮማንደር ብዙነህ አጎናፍር ÷ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል ብለዋል።

ይህም በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ በመሰራቱ ነው ብለዋል ኮማንደሩ።

በ13ቱ የምርጫ ክልሎችና 1ሺህ 128 ጣቢያዎች ላይ የተሰራጩ ቁሳቁሶች ችግር እንዳይገጥማቸው ሰርተናል ነው ያሉት።

ከምርጫው ጋር ተያይዞ ጥቃቅን ችግሮች እንደነበሩ ግን አንስተዋል።

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ እናት ፖርቲ እጩ ፍርድቤት ቀርቦ 8ሺህ ብር መቀጣቱን ተናግረዋል።

መንዝ ቀያ ላይም አንድ የብልፅግና እጩ ተወዳዳሪ ሲቀሰቅስ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ለምርጫው ሰላማዊነት ከፀጥታ ሃይሉ ባሻገር ማህበረሰቡም ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረው ተናግረዋል።

በቀጣይም ሰላሙን በራሱ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በሳምራዊት የስጋት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!