የሀገር ውስጥ ዜና

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የድምፅ ቆጠራ ተጠናቆ ለምርጫ ክልሎች እየተረከበ ነው

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራውን በማጠናቀቅ ለምርጫ ክልሎች እያስረከቡ ነው።

በክፍለ ከተማው ምርጫ ክልል 24 ከሚገኙት 160 ጣቢያዎች ወደ 60 የሚጠጉት እስካሁን ቆጠራውን አጠናቀው ማስረከባቸውን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ፈንታሁን አበራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ቀሪዎቹም ጣቢያዎች እስከ ምሽት ድረስ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በትእግስት ስለሺ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!