የሀገር ውስጥ ዜና

በወላይታ ዞን ሁሉም ድምፅ የተሰጠባቸው ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልሎች ደርሰዋል

By Meseret Awoke

June 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በወላይታ ዞን ድምፅ የተሰጠባቸው ሳጥኖች በሙሉ ወደ ምርጫ ክልሎች መድረሳቸው ተገለፀ።

በወላይታ ዞን በሰባት የምርጫ ክልሎች በ563 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሂደት ተከናውኗል፡፡

ድምፅ የተሰጠባቸው ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልሎች መድረሳቸውን እና ቆጠራና ርክክብ እየተደረገ መሆኑን የወላይታ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ስምኦን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬት ተናግረዋል ።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በማስተዋል አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!