ዓለምአቀፋዊ ዜና

በካናዳ በትምህርት ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የማይታወቁ መቃብሮች ተገኙ

By Meseret Awoke

June 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የሚገኝ አንድ ቡድን በ ሳስኬችዋን አውራጃ ውስጥ የቀድሞ የመኖሪያ ቤት ትምህርት ቤት በሚገኝበት ቦታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምልክት የሌላቸውን መቃብሮች ማግኘቱን ገለጸ፡፡

ባሳለፍነው ወር ካውስስ በሳስኬችዋን ግዛት በሚገኘው የማሪቫል የህንድ መኖሪያ ትምህርት ቤት የመቃብር ስፍራ ውስጥ ያልታወቁ መቃብሮች ለማግኘት መሬት ላይ ዘልቆ የሚገኘውን ራዳር ተጠቅመዋል፡፡

በትምህርት ቤት ላይ የተገኘውን የመቃብር ቁጥር በትክክል ያልተገለፀ ቢሆንም መቃብር መገኘቱ ዘግናኝ እና አስደንጋጭ ነው ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ዝርዝር ሁኔታዎች ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡

በብሪታንያ ከሳምንታት በፊት የ215 ልጆች ቅሪት መገኘቱንም መረጃው አስታውሷል፡፡

ምንጭ ፥ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!