ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

By Tibebu Kebede

June 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ቢሮው ድጋፍ ያደረገው በአጣዬ እና በመተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ነው፡፡

ቢሮው ድጋፍ ያደረገው በአጣዬ እና በመተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ነው፡፡

የቢሮው የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ፥ ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ተሰባስበው ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ማለታቸውን ከገቢዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!