የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ሉክዘምበርግ ተደራራቢ ቀረጥን ለማስቀረት ስምምነት ተፈራረሙ

By Tibebu Kebede

June 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሉክዘምበርግ ተደራራቢ ቀረጥን ማስቀረት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ እና የሉክዘምበርግ የገንዘብ ሚኒስትር ፒዬር ግራሜግና ተፈራርመውታል፡፡

በወቅቱ ሃገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ስምምነቱ የሃገራቱን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማጠናከር በቀረጥና ተያያዥ የግብር ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር እንደሚያግዝ መገለጹን በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!