የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው

By Tibebu Kebede

June 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 25፣2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በተያየዘ ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መስጠት ተጀምሯል።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 53 የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ፈተናው እየተሰጠ እንደሚገኝ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ ቡድን መሪ ሙሉጌታ ካሣ ለአሚኮ ተናግረዋል።

ተፈታኞች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 የትምህርት ዘመን ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት በሚፈለገው መልኩ ያልተማሩ በመሆኑ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የማካካሻ ትምህርት ሲሰጡ ቆይቷል ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!