የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከርኩ ነው-የሳይንስ እና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስቴር

By Tibebu Kebede

June 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከረ መሆኑን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ማምሻውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ በወጣው መረጃ÷በትግራይ ክልል የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በተመለከተ ከባለ ድርሻ አካላት እና ተቋሟት አመራሮች ጋር እየተወያየ መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም የተማሪዎች ቤተሰቦች የሚወሰነውን ውሳኔ በትዕግስት እንዲጠብቁ ነው ሚኒስቴሩ የጠየቀው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!