የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ19 ክትባትን በጋራ ማምረት በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

July 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ19 ክትባትን በጋራ ማምረት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ እና ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ ጋር በጤናው ዘርፍ በጋር መስራት በሚቻልባቸው አግባቦች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሃገራቱ በጋራ የኮቪድ19 ክትባትን ማምረት በሚችሉበት አግባብ ላይ፣ በአቅም ግንባታ፣ በጤናው ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!