አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍጋኒስታን የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ባግራም የተሰኘውን የጦር ሰፈር ለቆ መውጣቱ ተገልጿል፡፡
ወታደሮቹ ስፍራውን ለቀው የወጡት ዋሽንግተን ከታሊባን ጋር በገባችው ስምምነት መሰረት መሆኑን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ለ20 ዓመታት በአፍጋኒስታን ሰላም በማስከበር ሂደት ላይ የቆዩት የአሜሪካ እና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደሮች ባግራም የተሰኘውን የጦር ሰፈር በዛሬው ዕለት ለቀው መውጣታቸው ተገልጿል፡፡
ወታደሮቹ የጦር ሰፈሩን ለቀው መውታጣቸውም አሜሪካ በአፍጋኒስታን የነበራት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማብቃቱን ያረጋግጣል ነው የተባለው፡፡
አሁን ላይም የጦር ሰፈሩ በአፍጋኒስታን መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በጦር ሰፈሩ ከ2 ሺህ 500 እስከ 3 ሺህ 500 የሚደርሱ የአሜሪካ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ይኖሩ ነበር፡፡
ምንጭ፦ ሬውተርስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡