የሀገር ውስጥ ዜና

ከኢትዮጵያ ተሰርቀው ወደ ሆላንድ የተወሰዱ ጥንታዊ ቅርሶች ሊመለሱ ነው

By Tibebu Kebede

July 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ ተሰርቀው ወደ ሆላንድ የተወሰዱ ጥንታዊ ቅርሶች ሊመለሱ ነው፡፡

ቅርሶቹ የዛሬ ሳምንት በኔዘርላንድስ ለጨረታ ሊቀርቡና ሊሸጡ እንደነበር በኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲውም የጨረታ ሂደቱ እንዲቋረጥ ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ማግኘቱንም ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ቅርሶቹን የተረከበ ሲሆን፥ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን መንገድ እያመቻቸሁ ነው ብሏል፡፡

ቅርሶቹ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ይታመናል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!