የሀገር ውስጥ ዜና

በህወሃት የወደመውን የተከዜ ድልድይ የሚተካ ወታደራዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለማቅረብ እየተሰራ ነው-የመከላከያ ሠራዊት

By Tibebu Kebede

July 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት በህወሃት የሽብር ቡድን የወደመውን የተከዜ ድልድይ ለመተካት ወታደራዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ለድልድዩም አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያስታወቀው።

ሕወሃት የተከዜን ድልድይ ያወደመው የፌዴራል ሠራዊት እንዳይገባ ለማድረግ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች እርዳታውን በአውሮፕላን እንዲያደርሱ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡