አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከእምነ በረድ አምራቾች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ የማዕድን ሃብት በብዙ መልኩ የሚገለጽ መሆኑን ኢንጅነር ታከለ ኡማ አብራርተዋል፡፡
ብዙ መልክ ያለውን የማዕድን ሃብት በአግባቡ መጠቀም ደግሞ ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የእምነ በረድ አምራቾች በበኩላቸው ከመሰረተ ልማትና ከጸጥታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ለተነሱ ችግሮች መፍትሄ እንደሚፈልግ አረጋግጧል።
አምራቾቹ በቀጣይ ምርታቸውን በማሳደግ ከሀገር ውስጥ ምርት አቅርቦት አልፈው ለውጪ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ መግባባት ላይ መደረሱንም ኢንጅነር ታከለ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!