Afghan security personnel patrol during fighting between Taliban and Afghan security forces in Kunduz city, north of Kabul, Afghanistan, Thursday, June 24, 2021. Taliban gains in north Afghanistan, the traditional stronghold of the country's minority ethnic groups who drove the insurgent force from power nearly 20  years ago, has driven a worried government to resurrect militias whose histories have been characterized by chaos and widespread killing. (AP Photo/Samiullah Quraishi)

ዓለምአቀፋዊ ዜና

የታሊባን ሀይሎች በአፍጋኒስታን ቁልፍ አካባቢዎችን እየተቆጣጠሩ ነው

By Meseret Demissu

July 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍጋኒስታን ወታደሮች ወደ ጎረቤት ታጂኪስታን መሸሻቸውን ተከትሎ የታሊባን ሃይሎች ባዳክህሻን እና ካንዳሃር አካባቢ የሚገኙ አስተዳደራዊ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል።

የታሊባን ተዋጊዎች ወደ ድንበሩ ሲያቀኑ ከ300 በላይ የአፍጋኒስታን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን የባዳክህሻን ግዛት ወደ ታጂኪስታን መሻገራቸውን የታጂኪስታን ብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

”በመልካም ጎርብትና እና በሰብዓዊነት ” መርህ ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉትን የአፍጋኒስታን ወታደሮች ወደ ታጃኪስታን ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ መፍቀዳቸውን ባለስልጣናቱ በመግለጫቸው አክለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍጋኒስታን “የዘላለም ጦርነት” አብቅቷል ብለው ካወጁ ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ የታሊባን ሃይሎች በመላ ሃገሪቱ መስፋፋታቸው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ወሣኝ የሚባሉ ቦታዎችን የተቆጣጠሩት በሰሜናዊ አፍጋኒስታን ግማሽ ክፍል ሲሆን÷ ይህም በፈረንጆቹ 2001 የአፍጋን ወታደሮች ታሊባንን ለማሸነፍ የረዳቸውና የአሜሪካ መራሹ ጦር ምሽግ ነው ፡፡

ታሊባን በአሁኑ ጊዜ በአፍጋኒስታን ውስጥ ካሉት 421 አስተዳደራዊ አካባቢዎች 1/3 መቆጣጠሩ ይነገራል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!