የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በ2ተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

By Meseret Awoke

July 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሁለት ዓመታት በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች አስመርቋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባ-ገዳዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተመራቂዎቹ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

በአዲስ መልክ የተዋቀረውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ መርቀው መክፈታቸውን ኢዜአ አስታውሶ ዘግቧል።

አካዳሚው በሱሉልታ ከተማ በ40 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን፥ አጠቃላይ የግንባታ ወጪው 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!