የሀገር ውስጥ ዜና

የቻይናው ትያንጂን ማይወይ ኢንተርናሽናል የግል ኩባንያ ለፌዴራል ፖሊስ የፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

July 06, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ትያንጂን ማይወይ ኢንተርናሽናል የግል ካምፓኒ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኩባንያው 22 ሚሊየን 800 ሺህ ብር የሚገመቱ የፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎችን ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

በአሁኑ ወቅት ተቋሙ ለፀረ-ፈንጅ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት በተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና ትላልቅ ተቋማት ላይ በማሰማራት በዘመናዊ መሳሪያዎች የተደገፈ ፖሊሳዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎቹ በተጨማሪ በሰለጠኑ የፈንጅ አነፍናፊ ውሾች በመታገዝ ከፀረ-ፈንጅ ባለሙያዎች የተሰወሩ ነገሮችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፀረ-ፈንጅ መሳሪያዎቹ የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር ለመመከት እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለፅ ÷ኩባንያው ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የፀረ-ፈንጅ ምክትል ዳይሬክቶሬትም መሳሪያዎቹን በአግባቡ በመጠቀም ለተፈለጉለት አላማ እንዲያውላቸው አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።