የሀገር ውስጥ ዜና

ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 196 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

July 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 196 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች በስፋት ለመመለስ በታያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ገልጿል።

በዚህም 196 ሴቶችና 88 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 196 ተመላሾች ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!