አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር ከ1 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው ፡፡
በአንድ ጀንበር ከ1 ሚሊየን በላይ የችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጺዮን ተሾመ ÷ “ኑ አዲስ አበባን እናልብስ” በሚል ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በተለያዩ ስፍራዎች እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአንድ ጀንበር ከ1 ሚሊየን በላይ ችግኝ የመትከል መርሐግብር የፊታችን እሁድ ሀምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም በመላው አዲስ አበባ እንደሚካሄድ ኢንጂነር ጺዮን ተናግረዋል፡፡
ለመርሐግብሩ የሚሆን የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ቁፋሮን ጨምሮ ሀገር በቀል እና ለምግብነት እንዲሁም ለአካባቢ ውበት የሚጠቅሙ ችግኞች ከወዲሁ ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣የስፖርት ቤተሰቦች፣የሀይማኖት አባቶች ፣የጸጥታ አካላት ፣ወጣቶች እና ልዩ ልዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ዋና ዳይሬክተሯ መጠቆማቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!