አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ ዓረቢያ 2 ሺህ 536 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 333 ሴቶችና 161 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 536 ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ አቀባበል ያደረገላቸው መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!