አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ሂደቱንና ውጤቱን በማብራራት ላይ ናቸው።
ቦርዱ እንደገና ተዋቅሮ ወደ ስራ እንዲገባ በጀት በመመደብ መንግስትና ምክር ቤቱ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል ነው ያሉት።
የኮቪድ ተፅዕኖ የምርጫ ሂደቱን ማዘግየቱን ተናግረዋል።
ቦርዱ የምርጫውን ተዓማኒነት የሚጨምሩ ቁሳቁሶች ተጠቅሟል።
ለቁሳቁሶችም ከ845 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል ነው ያሉት።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ችግር በመራጮች ምዝገባ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል።
152ሺህ በላይ የምርጫ አስፈፃሚዎች ከ42 ሺህ በሚበልጡ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰማርተዋል።
72 መገናኛ ብዙኀን ምርጫውን ዘግበዋል ነው ያሉት።
ድምፅ መስጫ ቀን 40 ሺህ 365 ምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ እንደተሰጠባቸውም አስረድተዋል።
በ70 ምርጫ ጣቢያዎች ግን ድምፅ አልተሰጠምም ብለዋል።
ከምርጫው እጩዎች መካከል 99 ያህሉ አካል ጉዳተኞች ናቸው።
165 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ ቀርቦ ውጤት የሚቀይሩት ላይ ቦርዱ ውሳኔ ሰጥቷል።
በ10 የምርጫ ክልሎች ድጋሜ ቆጠራ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን 3ቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
ቦርዱ ያስዘገባቸው ስኬቶች መካከል ከወገንተኛ ፖለቲካ ነፃ መሆኑ፣ አዳዲስ አሰራሮችን ማስተዋወቁ፣ ተከታታይ ውይይቶችን በማዘጋጀት አመኔታውን መጨመሩ ነው ብለዋል ምክትል ቦርድ ሰብሳቢው።
በአፈወርቅ እያዩ