አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሊያ ፕሬዚደንት መሃመድ ፋርማጆ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚደንቱ በመልዕክታቸው ‘‘ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ ይሁንታ እንደገና በማግኘትዎ እንኳን ደስ አለዎት’’ ብለዋል፡፡
ሃገራቸው ሶማሊያ የሁለቱን ህዝቦች እንዲሁም ቀጠናውን ተጠቃሚ ለማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መስራቷን ትቀጥላለችም ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ ፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ‘‘ትልቅ ስኬት እመኛለሁ’’ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!