አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሮቤ ከተማ የተቀናጀ መናሃሪያ ተመርቋል።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት እና የከተማ ልማት ክላሰተር አስተባባሪ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የሮቤ ከተማን የተቀናጀ መናሃሪያ መርቀው ከፍተዋል።
የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ለህብረተሰቡ ዘመናዊና ተደራሽ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት 11 የመነሃሪያ ፕሮክጅቶችን በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከነዚህ ውስጥ በ290 ሚሊየን 600 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰራው የሮቤ ከተማ የተቀናጀ መናሃሪያ አንዱ ሲሆን÷ በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
መናሃሪያው በአንድ ጊዜ 200 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን÷ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩም ተመላክቷል።
በተጨማሪም መናሃሪያው የባንክ አገልግሎት፣የቴሎኮም አገልግሎት፣የተለያዩ ቢሮዎችና ሱቆች ፣ ጋራዥ እና የመንገደኞች ማረፊያ ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።
መናሃሪያው ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑም ተገልጿል።
በምርቃቱ ላይ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውም ነው የተገለጸው።
በከፍያለው ሽፈራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!