አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙት ባለፈው ሳምንት ከሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም የገቢ ኮንትሮባንድ 31 ሚሊየን 59 ሺህ 580ብር፤ በወጪ ደግሞ 550ሺህ 931 ብር ግምት እንዳላቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ከተያዙት እቃዎች መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን ÷ሶስት ተርጣሪዎች እና ታርጋ ቁጥር የሌላቸው አራት ሞተሮችን ጨምሮ 11 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!