የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

July 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት ለመመስረት የሚያስችልዎትን ድምጽ በማግኘትዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

በመልዕክታቸውም “በእርስዎ መሪነት ወዳጅ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ጊዜ የሚበለጽግና ዘመናዊ ዕሴቶችን የሚቀበል ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ለዓለም እያሳየ ይገኛል” ይገኛል ማለታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!