አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ለ313 ዲፕሎማቶች ለዲፕሎማቶች የሙያ መሰላል ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
የሙያ መሰላል ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ የተሰጠው በውጭ ግንኙነት ማሰልጠና ተቋም ከሶስተኛ ጸሐፊ እስከ አማካሪ አንድ ድረስ ባለው የሙያ እርከን ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ በውጭ ጉዳይ ዋናው መስሪያ ቤት እና በሚሲዮኖች ለሚገኙ 313 ዲፕሎማቶች ነው።
የምስክር ወረቀቱን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታአምባሳደር ብርቱካን ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዲፕሎማቶቹ ስልጠናውን በብቃት ተከታትለው በማጠናቀቃቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አያይዘውም ዲፕሎማቶቹ በተለያዩ እርከኖች ያገኙትን የዲፕሎማሲ ዕውቀት እና ክህሎት ተጠቅመው አገራቸውን ከመቼውም ጊዜ በበለጥ ቁርጠኛ ሆነው ማገልገል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
ዲፕሎማቶቹ በንድፈ ሃሳብ መረጃ የወሰዱትን ስልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ የአገርን ጥቅም በማስከበር ተግተው እንዲሰሩ እና የዲፕሎማሲን ሥነ -ምግባር በመላበስ ዓለም ከደረሰበት ዘመናዊ ዲፕሎማሲ ጋር እራሳቸውን አጣጥመው መሄድ እንደሚኖርባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት÷ አገራቸውን በዲፕሎማሲ ዘርፍ ለማገልገል ዕድሉ ስለገጠማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በቀጣይም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር ለውጠው አገራቸውን በቁርጠኝነት ለማገልገል ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!