የሀገር ውስጥ ዜና

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ቤተሰቦችን የቤት እድሳት የማስጀመር መርሀ ግብር አከናወነ

By Meseret Awoke

July 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ቤተሰቦችን የቤት እድሳት የማስጀመር መርሀ ግብር አከናውኗል።

ፋና ከሚያደርገው የመረጃ ተደራሽነት ባለፈ በበጎ ስራ ላይ በመሳተፍ አርአያ መሆን እንዳለበት የፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ገልፀዋል።

ይህ የበጎ ስራ በዚህ ብቻ የሚቆም ሳይሆን በሌሎችም የማህበረሰብ ድጋፍ ላይ በይበልጥ በመሰማራት ተቋሙ ጠንክሮ እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

በቅድስት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!