አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ለአሸባሪው ትህነግ ትንኮሳ የማያዳግም ምላሸ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የአሸባሪው ቡድን አባላት “በአማራ ሕዝብ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን” ማለታቸው ይታወሳል።
የማይካድራ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ለአሸባሪው ትህነግ የማያዳግም የአጸፋ መልስ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
“አካባቢያችንን እያለማን ለሀገራችን ዘብ እንቆማለን” ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ፥ በመስዋእትነት የተገኘውን ሕዝባዊ ነጻነት ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚወጡም ነው የተናገሩት።
የአሸባሪው ቡድን ርዝራዦች በማይካድራ የፈጸሙትን ግፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አይኑን ጨፍኖ እንዳላየ፣ ጆሮውን ደፍኖም እንዳልሰማ ማለፉ እንዳሳዘናቸው የገለጹት ነዋሪዎቹ፥ ለአሸባሪው ቡድን ወግኖ እንደተበደሉ ተደርጎ ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ማድረግ ተገቢነት የለውም ብለዋል።
ለዚህም መንግሥት ጠንካራ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚጠበቅበት፣ መገናኛ ብዙኃንም እውነታውን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስገንዘብ እንዳለባቸው ነዋሪዎቹ መናገራቸው አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!