አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ከዲጂታል ኢኮኖሚው ሀብት ማመንጨት የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሃመድ ገለጹ።
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ወደ ዕውቀት-መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ሀሳብ የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የትምህርት እና ሥልጠና ጥራትን ለማሳደግ ያለው ሚና፤ የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ለማሳደግ ሀገራዊ የዲጂታል ክህሎት የድርጊት መርሃ-ግብር፤ ቴክኖሎጂ የትምህርት፣ ምርምር እና የአስተዳደር ስርዓቱን ለማሳደግ ያለው ሚና፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በስራ ዕድል ፈጠራና እና ዲጂታላይዜሽን የግሉ ዘርፍ አበርክትዎ እንዲሁም ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን 2025 የሰውን ግንባታ እና የሴቶች ሚና በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታው በዲጂታል ኢኮኖሚ ዓለም አቀፉንና ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታው ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አመላክተዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂን ከፋይናንስ፣ ከኢኮኖሚና ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር አገናኝቶ ማየት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ከዲጂታል ኢኮኖሚው ሀብት ማመንጨት የሚያስችል አቅም መፍጠር የግድ የሚለው ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ተከትሎ ዲጂታል ኢኮኖሚው በሪፎርሙ ከተካተቱ አበይት ጉዳዮች አንዱ መሆኑንና ይህንን መሰረት በማድረግ ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ አንቂ የሆኑ ህጎችና መመሪያዎች ተሻሽለዋል ማለታቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!