የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን የፊታችን ቅዳሜ ያካሂዳል

By Tibebu Kebede

July 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክር ቤቱ የፕሬስ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ በሚያካሂደው 8ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎችን አብራርተዋል፡፡

መደበኛ ጉባኤውም የ2013 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደሚመክር ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።

በተጨማሪም የ2014 በጀትን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡

የአስተዳደሩ የኦዲት ግኝት ሪፖርትም ለምክር ቤቱ እንደሚቅርብና ሰፊ ውይይት እንደሚደረግበት መናገራቸውን የከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!