አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው ህወሃት ጋር እየተደረገ ያለውን የህልውና ዘመቻ ተከትሎ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ መኮንን እንዳሉት፥ ከመንግስት ሰራተኛው የወር ደመወዝ 254 ሚሊየን ብር ተገኝቷል።
በቀጣይም ከነጋዴው ማህበረሰብ እና ከግል ተቋማት ተጨማሪ ሃብት ለማሰባሰብ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፥ በሌላ በኩል 2ሺህ የሚሊሻ አባላትን ወደ ዘመቻ መላኩንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን የዞኑን ሰላም ለማስጠበቅ የጸጥታ ኃይሉ እየሰራ መሆኑም ተነግሯል።
በሙሉቀን አበበ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!