አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአሜሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ካሮሊን ራያን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በኤች ኤይ ቪ ኤድስ፣ በክትባት፣ ለህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት አግባብ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የላቦራቶሪዎችን አቅም ማሳደግ እንዲሁም አዳዳስ ትብብር ማድረግ በሚቻልባቸው የጤና መስኮች ዙሪያ መምከራቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!