የሀገር ውስጥ ዜና

ወደ ትግራይ ለሚገባ ሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊውን ፍተሻ ለማድረግ የሚያስችሉ ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች እየተተከሉ ነው

By Tibebu Kebede

July 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትግራይ ክልል የሚገባ ማንኛውም ሰብአዊ ድጋፍ ተገቢው ፍተሻ ተደርጎለት በአፋጣኝ ለተረጅዎች እንዲደርስ ለማስቻል ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች እየተተከሉ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በሰጡት መግለጫ ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን የያዙ 61 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቐለ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ሌሎች ተመሳሳይ ቁሳቁሶችን የጫኑ 60 ከባድ ተሽከርካሪዎችም በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ በመግባት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ወደ ትግራይ የሚገባ ማንኛውም ሰብአዊ ድጋፍ ተገቢው ፍተሻ ተደርጎለት በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች ተከላ በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!