የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

July 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በመልዕክታቸውም፥ እዉነትን ይዘን በራሳችን አቅም ድህነትን ድል ለመንሳት የጀመርነው መንገድ ፍፃሜው ላይ እየደረሰ ይገኛል፡፡

”መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም በመላው አለም የምትገኙ የአገሬ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!