የሀገር ውስጥ ዜና

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ለኢድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳቹህ መልእክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

July 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ለ1 ሺህ 142ኛው የኢድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳቹህ መልእክት አስተላለፉ፡፡

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ለመላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለ1 ሸህ 442ኛው የኢድ አል አድሀ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር እለት መሆኑንም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉም እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በተከተለ መልኩ ሊሆን እንደሚገም ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ ሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፥ በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችንበመርዳት እና አብሮነትና መደጋገፍን በማጎልበት ሊሆን ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1 ሺህ 442ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተደሰድሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው መላው የእምነቱ ተከታይ ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት አቅመ ደካሞችን በማገዝ እና በመርዳት በዓሉን ሊያከብር ይገባል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በእንኳን አደረሳችሁ መልክታቸው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በእስልምና አስተምህሮ መሠረት አንዱ ከሌላው በመተዛዘን እና በመደጋገፍ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር “እንኳን ለ1 ሺህ 142ኛ ለኢድ አል-አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ መጪው ጊዜ የሰላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ” ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ደግሞ፣ “በዓሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ድርብ ደስታ ነው” ብለዋል፡፡

የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ይህንን ታላቅ ክብረ በዓል በሚያከብርበት ጊዜ እንደተለመደው በመረዳዳት፣ በመተዛዘን፣ በንስሃ እና በፍቅር እንዲሆን ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!