የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

July 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በመልዕክታቸውም “የኢትዮጵያ ሀገራችን ብርቱ ልጆች ያለባቸው ከፍተኛ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫና ሳይበግራቸው ግድባችንን እዚህ ደረጃ ማድረሳቸው እጅግ ያስመሰግናቸዋል” ብለዋል።

በፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት “ለመላው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌት ተቀን በግድቡ ሥራ ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ በራሴ እና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ” ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!