አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የአንድነታችን ምልክትና የጋራ አሻራችን የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁና የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ በጥሩ ሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑ የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የአንድነታቸው የድል ውጤት ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
የምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ፥ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የታየው አንድነት በሁሉም መስኮች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!