አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ፌዴራል ፖሊስ ለመላው ህዝበ ሙስሊም እንኳን ለ1 ሺህ 442ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ይህ ታላቅ በዓል በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም ፌዴራል ፖሊስ ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
በዓሉ ሁለተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በስኬት በሰላም በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር በዓል በመሆኑ ደስታውን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።
መላው የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኃይል ከሌሎች ፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጅት ያደረጉና በወትሮ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውንም አስገንዝቧል።
መላው የኢስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር በደስታ እና በፍቅር እንዲከበር ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በማለት ተቋሙ ጥሪውን አቅርቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!