የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክርቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

July 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክርቤት የ5ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ፡፡

ምክር ቤቱ በክልሉም ሆነ በሃገራችን በተፈጠሩ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮች ለደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባዔውን ማካሄድ የጀመረው፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆውን ጉባዔውን የውይይት አጀንዳዎችን እንዲሁም የ11ኛውን መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ ጀምሯል፡፡

በዛሬ የጉባዔ ውሎው በርዕሰ-መስተዳድሩ የሚቀርበውን የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም በማድመጥ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!